ሰበር የምሽት:- በወሊሶ፣ በሆለታ፣ በበደኖ፣ በሙገር፣ በነጆ እና በነቀምቴ ከተሞች ተቃውሞው ቀጥሏል

3 Dec

አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በመቃወም በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም በወሊሶ፣ በሆለታ፣ በበደኖ፣ በሙገር፣ በነጆ እና በነቀምቴ ከተሞች መቀጠሉ ተሰማ::

ሊንኩን በመጫን ቪዲዮውን ይመልከቱ:-

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/48689

Hospitaltekawemo

እንደ ዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች ገለጻ በወሊሶ፣ በሆለታ፣ በበደኖ፣ በሙገር፣ በነጆ እና በነቀምቴ ከተሞች በሚገኙ ከፍተኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተቀጣጠለው ተቃውሞን ለመበተን ፖሊስ ሃይል ቢጠቀመምም የሕዝቡ ቁጣ አሁንም እንዳየለ ተገልጿል:: በበደኖ አደባባይ የወጣው ተቃውሞን ፖሊስ ለመበተን በወሰደው እርምጃ በርካታ ተማሪዎች መጎዳታቸውን የደረሰን መረጃ ሲያመለክት በተመሳሳይም በነጆ እና በነቀምቴም ፖሊስ ተማሪዎቹን ለመበተን በወሰደው እርምጃ መጎዳታቸውም ተሰምቷል:: በሆለታም እንዲሁም በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተነሳው ተቃውሞ ወጣት ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል:: ተቃውሞው ከፍተኛ እንደነበር የሚገልጹት ዘገባዎችም በርካታ ተማሪዎች በፖሊስ ቆመጥ መቀጥቀጣቸውን አስታውቀዋል:: የተማሪዎቹ ጥያቄ ከማስተርፕላኑ በተጨማሪ ፌደራል ፖሊስ እየፈጸመ ያለውን ግድያ እንዲያቆም የሚጠይቅም ሆኗል:: በሌላ በኩል በደቡብ ኦሮሚያ ቡሌ ሆራ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተነሳው ተቃውሞን ለማብረድ የተማሪዎች ተወካዮች እና የከተማው አስተዳደሮች ስብሰባ ቢቀመጡም ሊስማሙ አለመቻላቸው ታውቋል:: በወሊሶ፣ በሆለታ፣ በበደኖ፣ በሙገር፣ በነጆ እና በነቀምቴ ከተሞች አለመረጋጋቱ እንደቀጠለ ነው::

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: